መስከረም 20, 2018ዓ.ም በዛሬው ቀን በአ/ም/ዙ/ወ ቆላ—ሼሌ ቀበሌ አርሶአደሮች ጋር ስኬታማና አስደሳች ውይይት፣ እንዲሁም የስልጠና ጊዜን አሳልፈናል። more…..

አዲሱን የግብርና አብዮት ብዙዎች እየተቀላቀሉት ይገኛሉ።

በዛሬው ቀን በአ/ም/ዙ/ወ ቆላ—ሼሌ ቀበሌ አርሶአደሮች ጋር ስኬታማና አስደሳች ውይይት፣ እንዲሁም የስልጠና ጊዜን አሳልፈናል። (መስከረም 20, 2018ዓ.ም፣ ቆላ ሼሌ)

ዛሬ ከቆላ ሼሌ ሞዴል አርሶአደሮችና አመራር ጋር የጋራ ውይይት፣ የስልጠናና የምክክር መርሐግብር አካሂደናል። በአርሶአደሮች ህ/ሥ ዩኒየን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተካሄደው የምክክር ጉባኤ ከ35 በላይ የአርሶአደር ሞዴሎች፣ የቀበሌና የፓርቲ ጽ/ቤት አስተዳዳሪዎች፣ የልማት ባለሙያዎች እንዲሁም የከሃዝ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በፕሮግራሙም ለቀበሌው አርሶአደሮች፤
👉የመረጃ አስተራረስ (precision farming) ጥቅምና ብልጫዎችን፣
👉የወጪ ቆጣቢና ትርፋማ አስተራረስ ተግባራትን፣
👉የአፈር ምርመራ ማሠራት ምን ያህል የግብዓት ወጪ እንደሚያስቀር፣
👉እንዲሁም የKEHAZን ራዕይና አገልግሎቶችን በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።

አርሶአደሮችም “የሌተቀን ፈተናችንን ተረድታችሁ መላ ስላመጣችሁልን ደስ ብሎናል” ሲሉ ሀሳብና አስተያየታቸውን ሰጥተል። የአገልግሎቱ ዘላቂነትም እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ አሳስበውናል።

“KEHAZ guussi, lo7o shallaye guussako!”

በርካታ አርሶአደሮችም ወዲያውኑ በመመዝገብ የአርሶአደር ማህበረሰባችንን ተቀላቅለውታል፤ የእርሻቸውን አፈር ለምነት ለማስመርም ቀጠሮ አስይዘዉናል።ምስጋና፤ለቆላ ሼሌ ቀበሌ አስተዳደር፣ የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የልማት ባለሙያዎች፣ እንዲሁም አርሶአደሮች … አብራችሁን ሩቅ ስለምትጓዙ እናመሰግናለን።

በእኛው መላ!!
Our Own Solutions!!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *