Test your soil before planting, apply fertilizer, irrigation scheduling! ከዘር/ተከላ ወቅት፣ ማዳበሪያ ከመጠቀምዎ እንዲሁም ከመስኖ ተግባራት አስቀድሞ አፈርዎን ያስመርምሩ!!
Every farmer wants better yields, healthier crops, and peace of mind — but without knowing what your soil truly needs, you’re just guessing. That guesswork costs you time, money, and sometimes, your entire harvest. KEHAZ Soil Test Services help you break that cycle. Our service reveals exactly what your soil lacks (or has too much of), so you no longer overuse fertilizer, damage your soil, or waste resources. Whether you’re dealing with stunted growth, strange diseases, or unpredictable yields, a simple soil test can transform how you farm. The result? Higher productivity, smarter input use, stronger environmental balance — and less stress. Don’t just plant — plant with precision.
የአፈር ለምነት ምርመራ ምንድነው?
ዘመናዊ ግብርና የእርሻ አፈር ለምነትና ባህሪያትን በዝርዝር ለይቶ ከማወቅ ይጀምራል፡፡ የአፈር ለምነት ምርመራ የእርሻ አፈር ዓይነትን፣ pH ደረጃን፣ በውስጡ የሚገኙ ጠቃሚ ንጥረነገሮችን፣ የእርጥበትና የሙቀት ደረጃን እንዲሁም አጠቃላይ ለምነትን ለማወቅ የሚደረግ ቁልፍ ተግባር ነው፡፡ በዚህም መሠረት አርሶአደሮች የእርሻ ሥራቸውን በመረጃ በተደገፈ ሁኔታ እንዲመሩና ምርታማነታቸውን እንዲጨምሩ የሚያግዝ ሲሆን፣ የሚከተሉት ዋና ዋና ጥቅሞች አሉት፤
- ምርታማነትን ለመጨመር – የአፈሩን የለምነት ደረጃና ባህሪ ለይቶ በማወቅ፣ እንዲሁም ተስማሚ የሰብል ዝርያዎችን በመለየት ከፍተኛ ምርትን ለመሰብሰብ ያግዛል፡፡
- ወጪ ለመቀነስ – ለአፈሩ የሚያስፈልጉ የማዳበሪያ ግብዓቶችን ዓይነትና መጠንን ለይቶ በማወቅ ለተመጣጠነ የማዳበሪያ አጠቃቀም አቅጣጫ ይሰጣል፣ አላስፈላጊ የግብዓት ወጪዎችን ለማስቀረት ይረዳል፡፡
- የአፈር ጤንነትን በዘላቂነት ለመጠበቅ – የአፈሩን አጠቃላይ ጤንነት ደረጃን በየጊዜው በማወቅ የተሻለ የአፈር ለምነት አጠባበቅ ዘዴዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ያግዛል፡፡
- የሰብል ኪሳራ አደጋን ለመከላከል – የአፈሩን የለምነት ደረጃ አስቀድሞ በማወቅ ሊያስከትል የሚችለውን ዝቅተኛ ምርታማነትና ኪሳራን መከላከል ይቻላል፡፡